ወልቃይት ጀግኖቿን አመሰገነች።

0
317

ሑመራ፡ ጥር 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲሱ ትውልድ የትግል አርማ፣ የአማራ ሕዝብ የዘመናት ተጋድሎ መሰባሰቢያ ማዕከል እና የነፃነት አሻራ ምልክት ናት፤ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና የውጭ ዞምቤዎቹ አካባቢውን አብዝተው ይፈልጉታል። ይህን አካባቢ መልሰው በእጃቸው ለማስገባትም እስከ ሲኦል ለመውረድ የቻሉትን ሁሉ ሞክረዋል።

በዞኑ ከደርዘን በላይ ሙከራ አድርገው ህልማቸው የቀን ቅዥት የሆነባቸው የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች አቅጣጫቸውን ቀይረው በአማራ እና አፋር ንጹሃን ላይ ለመናገር የሚከብድ ግፍ፣ በደል እና ዘረፋ ፈጽመዋል።

ዞኑ ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ የሀገሪቱን ዳር ድንበር ለጠበቁ እና የአካባቢውን ሰላም በጽናት ላስከበሩ የአካባቢው የጸጥታ ኅይሎች እና የሚሊሻ አባላት የእውቅና እና የምሥጋና መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ርእሰ መዲና ሁመራ ከተማ ዛሬ በተካሄደው የእውቅና እና ምስጋና መርሐ ግብር ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው ሰላም አስከባሪዎቹን “የዘመኑ ጀግኖች” ሲሉ አሞካሽተዋቸዋል።

በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች የተፈጸመው ወረራ ግቡ እና ማዕከሉ የሁመራን ኮሪደር ማስከፈት ነበር ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በጥረታችሁ የጠላት ፍላጎት እና መሻት ከንቱ ሆኗል ነው ያሉት። አካባቢው በጥላት ያልተደፈረው ጠላት አካባቢውን ስለማይፈልገው ሳይሆን አቅሙን እና አቅማችንን ስለሚያውቅ ነው ብለዋል።

የተከፈተው ጦርነት ውስብስብ እና ዘርፈ ብዙ ነበር ያሉት አቶ አሸተ ከአፈሙዝ እስከ ዲፕሎማሲ፣ ከምጣኔ ሃብት እስከ ፕሮፖጋንዳ፣ ከተልዕኮ እስከ ፖለቲካ ጦርነት ኢትዮጵያ በብዙው ተፈትናለች ብለዋል። የጦርነቱ ተዋናዮችም የትግራይ ወራሪ ቡድን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ የዘመናት የውጭ ጠላቶች እና የውስጥ ተላላኪዎች ሁሉ የተሳተፉበት ነበር ብለዋል።

ጦርነቱ ገና አልተጠናቀቀም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ወልቃይት የውስጥ ባንዳዎች እና የውጭ ጠላቶች የዘወትር ምኞት መሆኗን አውቀን ነቅተን መጠበቅ አለብን ብለዋል። በአፋር እና በአማራ ክልል የሚቅበዘበዘው የጠላት ቡድን መቀበሪያው ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ይሆናል ነው ያሉት።

ባለፉት ወራት የነበረው ትግል ውጣ ውረዱ መራር ቢሆንም የመጀመሪያው ዙር በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቋል። በቀጣይም ከስህተቶቻችን ተምረን እና ጥንካሬዎቻችንን አስቀጥለን እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን እንቀጥላለን ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው። ይህ የምስጋና እና የእውቅና መርሐ ግብር ላለፈው ምሥጋና ለቀጣዩ አደራ ነውም ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው -ከሑመራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/