‘ወልቂ’ እና ‘ሃጫሉ’ የተባሉት አዲስ የባቄላ ዝርያዎች የተሻለ ምርት መስጠታቸው ተገለፀ።

0
252

ባሕር ዳር፡ መስከረም 24/2013ዓ.ም (አብመድ) በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ በባቄላ ሰብል ላይ እየደረሰ ያለውን የቆረመድ በሽታ ለመከላከል የሚችል አዲስ የባቄላ ዝርያ የተጠቀሙት አርሶ አደሮች የተሻለ ምርት ማግኘታቸውን ተናገሩ። አዲሶቹን ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች በስፋት ለማስተዋወቅም የመስክ ምልከታ እየተካሄደ ነው።

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ከፋርጣ ወረዳ ፀጉር ቀበሌ በተደረገው የመስክ ምልከታ ነው ቆረመድ የተባለውን በሽታ መከላከል የሚያስችል ‘ወልቂ’ እና ‘ሃጫሉ’ የተባሉትን አዲስ የባቄላ ዝርያ እያስተዋወቀ ያለው።

በመስክ ምልከታው የተገኙት የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጥላየ ተክለወልድ (ዶክተር) የባቄላ ቆርምድ በሽታ በሁሉም የክልሉ ወረዳዎች ጉዳት ሲያደርስ የነበረ መሆኑን አመላክተዋል። ለአዲሶቹ ዝርያዎች በሽታውን መቋቋም የሚችል ‘ኖብል 25’ እና ‘ሩዶሜን’ የተበሉ መድኃኒቶች ተዘጋጅተው ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በባለፈው ዓመት ለሠርቶ ማሳያ አዲስ የበቄላ ዝርያ ከምርምር ማዕከል ወሰወደው ከዘሩት አርሶ አደሮች ማሳ ሲታይም አዲሱ ዝርያ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል። በግል ገዝቶ ለመጠቀም አዲሱ ዝርያ ተደራሽ መሆን አለመጀመሩንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፤ በቀጣይ ከግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር ለአርሶ አደሩ ተደርሽ ለማድረግ እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡

ዘጋቢ: ብርቱካን ታዬ