ኮሮና ቫይረስ የዓለም የጤና ስጋት መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አወጀ፡፡

0
175

ባሕር ዳር፡- ጥር 22/2012ዓ.ም (አብመድ) ገዳዩ ኮሮና ቫይረስ በ21 ሀገራት እንደተከሰተ፤ ከ8 ሽህ በላይ ሰዎችም በበሽታው እንደተያዙ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ኮሮና ቫይረስ በቻይና ሁቤ ክፍለ ግዛት ውሃን ከተማ መከሰቱ ከተረጋገጠ በኋላ መዳረሻውን በማስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው ከቻይና ውጭ ባሉ 21 ሀገራት በሽታው ተከስቷል::

እስካለፈው ማክሰኞ ድረስ የወጡ ዘገባዎች እንዳመላከቱት በቫይረሱ 170 ቻይናውያን ህይዎታቸውን አጥተዋል፡፡ በበሽታው የተያዙት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ 8 ሽህ አሻቅቧል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 98 ሰዎች ብቻ ናቸው የሌላ ሀገር ዜጎች፤ ቀሪዎቹ ቻይናውያን ናቸው፡፡ ከቻይናውን ውጭ ግን ሕይዎቱ ያለፈ የውጭ ሀገር ዜጋ የለም ነው ያለው ድርጅቱ፡፡

በመሆኑም የዓለም የጤና ድርጅት አዲሱ ኮሮና ቫይረስ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የጤና ስጋት እንደሆነ አውጇል፡፡

ምንጭ፡- የዓለም የጤና ድርጅት ድረ ገጽ

በኃይሉ ማሞ