ክልሉ የገጠመውን የኅልውና አደጋ በአግባቡ በመመከት የሕዝቡን የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ ማድረጉን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።

0
391

የካቲት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ክልሉ የገጠመው የሰላምና የፀጥታ ችግሮችን በአግባቡ ለመቅረፍ ያስችል ዘንድ በክልሉ ያሉ የፀጥታ መዋቅሩ ላይ ያሉ ጉድለቶችን እና ጥንካሬወችን በዝርዝር ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቷል።

በመኾኑም ክልሉ የገጠመውን የኅልውና አደጋ በአግባቡ በመመከት የሕዝቡን የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ አድርጓል። ስለኾነም

1- የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር የፀጥታ አማካሪ

2- የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጀነራል መሠለ በለጠ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ኾነው ተሹመዋል።

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለአሚኮ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/