ካናዳ 132 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ልታበረክት ነው፡፡

0
56

ካናዳ 132 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ልታበረክት ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) በአነስተኛ የካርበን ልቀት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ለመገንባት እና የአየር
ንብረት ለውጥ የሚቋቋም የልማት ስትራቴጅን ለመከተል ካናዳ ከአፍሪካ ሀገሮች ጋር ተባብራ መሥራት የምትችልባቸውን
አማራጭ የሚያፈላልግ ሲምፖዚየም በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡
በሲምፖዚየሙ ላይ የተሳተፉት የፕላንና ልማት ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ የኢትዮጵያን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር
የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ለተሳታፊዎቹ አቅርበዋል፡፡
ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ችግሩን ለመከላከል በየዓመቱ የችግን ተከላ እያካሄደች መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በአፍሪካ እየተስፋፋ ያለውን በረሃማነትን ለመግታት እና በአደጉ ሀገሮች ምክንያት እየደረሰ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ
ችግሮችን ለመቋቋም እንደ ካናዳ ያሉ ያደጉ ሀገሮች በቴክኖሎጂና በገንዘብ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ የአረንጓዴ ልማትና የአየር ንብረትን ለመከላከል ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብር
አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የአከባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመድን
መሀመድ (ዶ.ር) በአረንጓዴ ልማት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በአነርጂ ዙሪያ የግል ባለሀብቶች በሚሳተፉበት ዙሪያ ማብራሪያ
ሰጥተዋል፡፡
የካናዳ ዓለም አቀፍ ሚኒስትር ካርና ጉድ ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ 132 ነጥብ 9 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማበርከት ቃል
ገብተዋል፡፡
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ልዩ አማካሪ ዶክተር እውነቱ ኃይሉ
በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት ዕድሎች፣ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል ፤ ባለሃብቶችም
ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ጋብዘዋል፡፡
በሲምፖዝየሙ በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፣ በካናዳ የሴኔጋል ኤምባሲና የካናዳ ውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስቴር
ባዘጋጁት መድረክ ላይ 35 የአፍሪካ ሀገሮች በበይነ መረብ ተሳትፈዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here