ከደሴ እስከ ወልድያ ያሉት ከተሞች ኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ።

76
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ

ጥር 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከደሴ እስከ ወልድያ ሲከናወን የቆየው ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል መስመሮች የመጠገን ሥራ ትናንት ምሽት ተጠናቆ ከተሞቹ ከ 10:05 ጀምሮ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

ጥገናው ትናንት ምሽት ቢጠናቀቅም መስመሩ በሚያልፍበት አካባቢ በደሴ እና በሐይቅ መካከል እንዲሁም መርሳ አካባቢ የበቀለ ዛፍ ከመስመሩ ጋር ተገናኝቶ ባለመቆረጡ የተነሳ ኤሌክትሪክ ማገናኘት አልተቻለም ነበር ብሏል።

ይሁንና ዛሬ ዛፎቹ በመቆረጣቸውና ኃይል ለመስጠት የሚያግድ ነገር ባለመኖሩ ከተሞቹ ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል።

ተቋሙ አያይዞም ለወልድያ ከተማና አካባቢው አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ የተዘረፈው ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ የሚሰጠውን አገልግሎት የሚተካ ዘላቂ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

የተጀመረው ሥራ በቀጣዮቹ ከአራት እስከ አምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ከፍተኛ ኃይል ለመስጠት የሚያስችል ነው ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/