ከውጭ የሚገባን ስንዴ ከ50 በመቶ በላይ ለመቀነስ እየሠራ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

885

ከውጭ የሚገባን ስንዴ ከ50 በመቶ በላይ ለመቀነስ እየሠራ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር፡ መስከረም 28/2013ዓ.ም (አብመድ) በ2013 ዓ.ም በሀገሪቱ 300 ሺህ ሄክታር መሬት ስንዴ በመስኖ ለማልማት መታቀዱን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡ የፌዴራል እና የአማራ ክልል የግብርና የሥራ ኃላፊዎች በምዕራብ ጎጃም ዞን በቆጋ መስኖ ፕሮጀክት ለቆላ የስንዴ ምርት የተዘጋጀ የመስኖ ቦታዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

በአማራ ክልል 50 ሺህ 200 ሄክታር መሬት የቆላ ስንዴ ምርት በመስኖ ለማልማት መታቀዱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ መለሰ መኮንን (ዶክተር) ገልጸዋል፡፡ ከዚህም 2 ሚሊዮን ኩንታል ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከእርሻ ሥራ አስከ ሰብል መሰብሰብ የሚያገለግሉ ቴክኖሎጅዎችን ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑንም ዶክተር መለሰ ገልጸዋል፡፡

የፌዴራል ግብርና ሚስቴር ሚኒስትር ዑመር ሁሴን እንደገለጹት ደግሞ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከ1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በማውጣት 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ በዓመት ከውጭ ታስገባለች፡፡ ሀገሪቱ ለስንዴ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት በሀገር ደረጃ የቆላ ስንዴ በስፋት ለማምረት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

በ2013 ዓ.ም በሀገሪቱ 300 ሺህ ሄክታር መሬት የቆላ ስንዴ በመስኖ ለማምረት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ብርቱካን ታዬ