ከአሰላ ከተማ የሀገር ጥሪ ተቀብለው የመከላከያ ሠራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ።

0
61

ከአሰላ ከተማ የሀገር ጥሪ ተቀብለው የመከላከያ ሠራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ።

ባሕር ዳር: ሐምሌ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአሰላ ከተማ ሀገራዊ ጥሪውን በመቀበል የመከላከያ ሠራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ዛሬ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ወጣቶቹ ለሀገር ባላቸው ፍቅር እንዲሁም ከልጅነታቸዉ ጀምሮ ለመከላከያ ሠራዊት ባላቸዉ ክብር ሠራዊቱን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተናግረዋል፡፡

በስፍራዉ የተገኙ ወላጆችም የኛ የመኖር ህልውና በሀገር ሰላም መሆን ላይ የተመሰረተ ነውና ልጆቻችንን ለሀገር ሰላምና ሉዓላዊነት እንዲሰለፉ ሸኝተናል ብለዋል፡፡

የአሰላ ከተማ አስተዳደር እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሸምሰዲን መሐመድ በበኩላቸው የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ዝግጁ የሆኑ ወጣቶችን የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን እንዲቀላቀሉ መልምለናል ነው ያሉት፡፡

ወጣቱ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር ለመግለጽ እና ክብሯን ለማስጠበቅ ያሳየው ተነሳሽነትም የሚደንቅ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በልጆቻቸዉ ሲረዱ የነበሩ እና ልጆቻቸውን ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ የሸኙ ወላጆች ኅብረተሰቡ እንዲደግፋቸው ኀላፊው ጥሪ እንዳቀረቡ የዘገበው ፋብኮ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here