“ከተማዋ በኢንቨስትመንት ተደራሽት ብቻ ሳይሆን ለነዋሪዎቿ ምቹ በመሆን ተመራጭ እንደትሆን እየሰራን ነዉ” የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ካሳሁን እምቢዓለ

0
39

ደብረብርሃን፡ ጥር 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ የኢንቨስትመንት መዳረሻ የመሆኗ እድል እየጨመረና እየሰፋ መጥቷል፡፡ ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ካሳሁን እምቢዓለ “ደብረ ብርሃን ከተማ በአልሚዎች በኩል ተመራጭ የሆነች ከተማ ሆናለች” ብለዋል፡፡ አልሚዎች ኢንቨስት ለማድረግ የመጀመሪያ ፍላጎታቸዉ የሰላምና ደኅንነት ጉዳይ ነዉ ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባዉ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪ ለሰላም ያለዉ ቁርጠኝነት ደግሞ ባለሃብቶቹ በከተማዋ ላይ አይናቸዉን እንዲያሳርፉ አድርጓቸዋል ነው ያሉት፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ ከ300 በላይ የኢንቨስትመንት አማራጮች ወደ ተግባር እየገቡ ነዉ ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባዉ ከ30 በላይ የሚሆኑት ተጠናቀዉ ምርት ማረት እንደጀመሩ ተናግረዋል፡፡

“ከተማዋ በኢንቨስትመንት ተደራሽ ብቻ ሳይሆን ለነዋሪዎቿ ምቹ በመሆን ተመራጭ እንደትሆን እየሰራን ነዉ” ያሉት አቶ ካሳሁን እየመጡ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች በቀዳሚነት የከተማዋን ነዋሪዎች ጥቅም የጠበቁ እንዲሆኑ ተደርጎ እየተሰራ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡

ከአራት መቶ በላይ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች በአዲስ መልክ ቀርበዉ እታዬ ስለመሆኑም ነዉ አቶ ካሳሁን ከአሚኮ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ያብራሩት፡፡

“ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት መሆኑን የሚረዳ ማኅበረሰብ ስላለ ይህንን እሳቤ በማጠናከር ከተማዋ የበለጠ እድገት እንድታስመዘግብ እየሰራን ነዉ” ብለዋል ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባዉ፡፡

ወደ ከተማዋ እየመጣ ያለዉ ኢንቨስትመንት ከጥቂት ዓመታት በኋላ በኢንቨስትመንት ለሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ተምሳሌት እንድትሆን ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

አሳሪ የሆኑ አሰራሮችን በማስተካከል ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት አልሚዎች ለሚያቀርቡት ጥያቄ በአጭር ጊዜ መፍትሄ ለመስጠት መታቀዱንም ገልጸዋል፡፡

ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ከተላላኪዉ ሸኔ ጋር የሚደረገዉ የህልዉና ዘመቻ አልተጠናቀቀም ያሉት አቶ ካሳሁን ለአፍታም ቢሆን ሳንዘናጋ ጠላቶቻንን መቅበር ላይ አተኩረን ልንሰራ ይገባልም ብለዋል፡፡

የከተራ፣ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላት በከተማዋ ያለምንም የፀጥታ ችግር በመከበራቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎችን ያመሰገኑት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባዉ አሁንም ቢሆን ሰላማችንን ሊነጥቁን የሚሞክሩትን አካላት ልንታገል ይገባል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ:–ኤሊያስ ፈጠነ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/