በዚህ ሳምንት በስፖርቱ ዓለም ጥቁሮች በቤዝ ቦል ጨዋታ ላይ እንዳይሳተፉ ከታገዱበት ቀለበት ለመውጣት የቻሉበት ክስተት አስተናግዷል፡፡
ባሕርዳር: መጋቢት 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከሰላሳ ዓመታት በላይ የጥቁር ቤዝቦል ተጫዋቾች በዋና ቤዝቦል ሊጎች እንዳይሳተፉ ታግደው ቆይተዋል።
ይሁን እንጅ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የካቲት 13 ቀን 1920 ዓ.ም በዚህ ሳምንት ማለት ነው የተጣለባቸውን እግድ ሰብረው ለመውጣት ጥረት ያደረጉበት እና የራሳቸውን ቡድን ማቋቋም የቻሉበት ጊዜ ነበር፡፡
በዚህ ረገድ ልክ በዚህ ሳምንት በካንሳስ ከተማ ሩቤ ፎስተር የተባለ ጥቁር ግለሰብ እግዱን ወደ ጎን በመተው የራሱን ሊግ በማቋቋም የራሱን ቡድን መመስረት ችሏል፡፡
በምሥጋናው ብርሃኔ