ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ

155
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ
የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች
የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እየመከረ ነው።
በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጀው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ከትናንት ሕዳር 21 ጀምሮ ሽሬ ላይ ሥራውን ጀምሯል።
ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ታጣቂዎች የተውጣጣው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሥራውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይታመናል።
ኮሚቴው የሚያወጣው ዝርዝር ዕቅድ ትጥቅ የማስፈታት፣ ካምፕ የማስገባትና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመልስ ይሆናል።
ዝርዝር ዕቅዱን የማውጣት ተግባሩ፣ በቴክኒክ ጉዳዮች ምክንያት መዘግየቱ ይታወቃል።
ሕዳር 22/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት