“እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚሰፍነው በሀገራት ላይ ጣልቃ ገብነት ሲቆምና ህዝቡ የራሱ ዴሞክራሲ ባለቤት ሲሆን ነው”

0
66

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ አንድ የዴሞክራሲ ዓይነት ብቻ የለም፤ ይልቁንም እውነተኛ የዴሞክራሲ መንፈሥ ለማስፈን እንሥራ ሲሉ በ14ኛው የባሊ የዴሞክራሲ መድረክ ላይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዋንግ ዪ በበይነ መረብ በተካሄደው የዴሞክራሲ መድረክ ላይ እንደተናገሩት ቅድመ አያቶቻችን እኛ የሰው ልጆች ከጦርነት ነጻ የሆነ፣ ረሃብና ድህነት ያላገኘው፣ በፍትህ ላይ የተመሠረተ ደስተኛ ሕይወት እንድንኖር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ላለፉት ሺህ ዓመታት የተሻሉ ስርዓቶች እና የፖለቲካ አወቃቀሮች ላይ ሠርተዋል፡፡

ዛሬ ፈልገን የምናሳድደውን ዴሞክራሲ እነሱ ቀድመው ሰርተውታልም ብለዋል የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡

በበይነ መረብ በተካሄደው ውይይት ላይ አንድ የቻይና ዲፕሎማት በሰጡት አስተያየትም “አንዳንዶች የአንድን አገር የዴሞክራሲ ሞዴል እንደ አይነኬ መሥፈርት በመውሰድ ለመተግበር ሲጥሩ በዓለም የዴሞክራሲ ሥርዓቶች እና ርዕዮተ ዓለሞች መካከል ውጥረት በመቀስቀስ ለመለያየት እና ግጭት መንስኤ ሲሆኑ ይስተዋላል” ብለዋል፡፡

እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚሰፍነው በሀገራት ላይ ጣልቃ ገብነት ሲቆም እና ህዝቡ የራሱ ዴሞክራሲ ባለቤት ሲሆን ነው ማለታቸውንም ሲጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation