”እኔ ለወገኔ” በሚል መሪ ሀሳብ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው።

0
105

ባሕር ዳር፡ ጥር 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ”እኔ ለወገኔ” በሚል መሪ ሀሳብ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብሩን ያዘጋጀው ኢትዮ- ጀርመን ለኢትዮጵያ ኮሚቴ ሲሆን፤ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲያስፖራዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ታድመዋል፡፡

በመርሃ-ግብሩ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይም እያንዳንዱ ዲያስፖራ 12 ሺህ ብር በመክፈል የሚታደም ሲሆን ገቢውም ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ይውላል፡፡

ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚህን ወቅት መርሃ-ግብሩን ላዘጋጀው ኢትዮ- ጀርመን ለኢትዮጵያ ኮሚቴ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰው፤ በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን መደገፍ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኢዜአ እንደዘገበው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/