“እስከ አሁን ከአረብ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከታሰበው 102 ሺህ ዜጎች መካከል ግማሽ ያህሉን መመለስ ተችሏል” ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

0
55

ሐምሌ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በሳምንታዊ መግለጫቸው እንዳሉት በሚቀጥለው ሳምንት ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምሥራቅ 12 ሽህ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ።
በታንዛኒያ፣ ጅቡቲ፣ ኬኒያ፣ ኦማን የነበሩ ዜጎችም ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ብለዋል፡፡
126 በረራዎችን በማድረግ እስከ አሁን ከአረብ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከታሰበው 102 ሺህ ዜጎች መካከል ግማሽ ያህሉን መመለስ ተችሏል።
ከሰኔ 26 ጀምሮ ከዒድ እስከ ዒድ መርኃግብር ዜጎች ወደ ሀገር ቤት እንደገቡም አስረድተዋል።
በሴኔጋል ዳካር በነበረው የዓለም ባንክ ስብሰባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን በመገኘት ባንኩ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቷል። ድጋፉ በሦስት ዓመት ውስጥ የሚሰጥ ሲኾን የኢትዮጵያን ለውጥ፣ የግብርና እና ድህነት ቅነሳ እንዲሁም የመሠረተ ልማት ግንባታን የሚያግዝ ነው ተብሏል።
እንደ አምባሳደር መለስ ዓለም ገለጻ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ ሥራውን ጀምሯል፡፡
ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ለሚካሄደው ንግግር የራሱን የአሠራርና ሥነምግባር አካሄድ ተወያይቶ መወሰኑ ይታወሳል።
መንግሥት በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደነበረው ጉዳዩን በሰላም ለመፍታት እየሠራ ይገኛል። ይሁንና አሸባሪው የሕወሓት ቡድን አሁንም የጦርነት ጉሰማ እያደረገ የሚገኝ በመኾኑ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴ እንዲያስቆም አምባሳደር መለስ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
8 Comments