“እስከ ሕይወት መስዋእትነት ዋጋ በመክፈል አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ዝግጁ ነን” የደባርቅ ከተማ ወጣቶች

0
131

“እስከ ሕይወት መስዋእትነት ዋጋ በመክፈል አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ዝግጁ ነን” የደባርቅ ከተማ ወጣቶች

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 01/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ወጣቶች ማኅበር በህልውና ዘመቻው ማከናወን በሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ በደባርቅ ከተማ ምክክር አካሂዷል።

የአማራ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዓባይነህ ጌጡ ወቅቱ የኢትዮጵያ ጠላት የኾነውን አሸባሪው የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ በጋራ የምንነሳበት ነው ብሏል።

ወጣቶች የቀደምት ጀግኖችን ጀብድ በመፈጸም ኢትዮጵያን መታደግ ይገባቸዋል ነው ያለው። ለዚህም ወጣቶች ከጸጥታ ኀይሉ ጋር ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም ነው የገለጸው።

የደባርቅ ወጣቶች አካባቢያቸውን ከአሸባሪ ቡድኑ ተላላኪዎች በመጠበቅ እያደረጉ ያሉት ተጋድሎ የሚመሰገን እንደሆነም ተናግሯል።

በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ ሙሉቀን አዳነ (ዶ.ር) እንደተናገሩት አሸባሪው የትህነግ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየታተረ ነው፤ ሁሉም ወጣቶች በመደራጀት፣ በግንባር በመዝመትና አካባቢያቸውን ነቅቶ በመጠበቅ ኀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች እስከ ሕይወት መስዋእትነት ዋጋ በመክፈል አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ያጋጠመውን የህልውና አደጋ በድል ለመሻገር እንረባረባለን ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው- ከደባርቅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here