ኢትዮ ቴሌኮም የላቀ የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የአራተኛው ትውልድ “የ4 ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ” የኢንተርኔት አገልግሎት በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን አስጀመረ።

0
85

ኢትዮ ቴሌኮም የላቀ የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የአራተኛው ትውልድ “የ4 ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ”
የኢንተርኔት አገልግሎት በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን አስጀመረ።
ባሕር ዳር: ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን በሚገኙ የጎንደርና ደብረታቦር
ከተሞች ነው አገልግሎቱን ያስጀመረው።
በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን በሚገኙ የጎንደርና ደብረታቦር ከተሞች 361 ሺህ ሰዎች አገልግሎቱን ያገኛሉም ተብሏል።
ኩባንያው የአራተኛው ትውልድ (4ጂ) ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ ኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርኃግብሩን የተለያዩ አካላት
በተገኙበት በጎንደር ከተማ ዛሬ አስጀምሯል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የአራተኛው ትውልድ (4ጂ) አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና አስተማማኝ
የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ እንደመኾኑ ደንበኞች የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።
እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ እስካሁን በ67 ከተሞች የአራተኛው ትውልድ (4ጂ) ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ ማስፋፊያ ሥራዎች
ተከናውነው የኢንተርኔት አገልግሎቱ እየተሰጠ ነው። አገልግሎቱ ተደራሽ ባልሆኑባቸው የተለያዩ አካባቢዎች 4 ጂ የሞባይል ዳታ
በሂደት ለማሟላትና የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት ተጨማሪ የማስፋፊያ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ከ55 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት ከኩባንያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዘጋቢ፡- ኃይሉ ማሞ-ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here