ኢትዮጵያ የአፍሪካ አረጋውያን ፕሮቶኮልን አጸደቀች፡፡

115

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አረጋውያን ፕሮቶኮልን አጸደቀች፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) እ.ኤ.አ በ2016 የአፍሪካ ሕብረት 26ኛ መደበኛ ጉባዔ ካከናወናቸው ተግባራት አንዱ
አረጋውያንን በተመለከተ “በአፍሪካ ሕዝቦች እና ሰዎች መብቶች ቻርተር” የአፍሪካ አረጋውያን ፕሮቶኮል ማጽደቅ ነው፤ ይህም
ፕሮቶኮል እ.ኤ.አ ጥር 16/2020 ፀድቋል፡፡
ፕሮቶኮሉ በአፍሪካ የሚገኙ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ አረጋውያንን ፍላጎት በተመለከተ በልዩነት ትኩረት ሰጥቶ ለመተግበር
የሚያስችል መብቶቻቸውን እና ሊደረግላቸው የሚገባ ጥበቃን፣ አስመልክቶ አባል ሀገራት ሊውስዱት የሚገባቸውን ዕርምጃዎችን
ያካተተ ነው፡፡
ፕሮቶኮሉ ከያዛቸው የአረጋውያን መብቶች በዋናነት በማኀበረሰብ፣ በባህል ከተቀመጡ አስተሳሰቦች ጨምሮ ከማንኛውም
መድሎዎች ነጻ የመሆን መብት፣ ዕኩል የፍትሕ እና የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት፣ የራሳቸውን ደኅንነት አስመልክቶ ካለማንም
ጣልቃ ገብነት ውሳኔ የመወሰን፣ የጤና፣ የአካል፣ የልምድ፣ አቅማቸውን ያማከል የሥራ ዕድል ማግኘት መብት፣ ማኅበራዊ
ደኅንነት ጥበቃ መብት፣ ድጋፍና እንክብካቤ ማግኘት መብት፣ የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት እና ሌሎች መብቶችን
እንደያዘ ተገልጿል፡፡
ፕሮቶኮሉ በልዩ ሁኔታ ለሴት አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኛ የሆኑ አረጋውያን እና በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋ ስጋት ባለባቸው
አካባቢዎች የሚገኙ አረጋውያንን አስመልክቶ የተለያዩ ልዩ ልዩ ጥበቃዎችን የሚያስቀምጡ ድንጋጌዎችንም አካቷል፡፡
ይህ ፕሮቶኮል ለአረጋውያኑ እነዚህን መብቶች እንዲጠበቁላቸው ሲደነግግ በሌላ በኩል ለቤተሰባቸው፣ ለማኅበረሰብ፣ ለሀገር
ብሎም ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዕውቀታቸውን እና ልምዳቸውን እንዲያጋሩ፣ በአስማሚነት እና ግጭት በመፍታት ሂደት ተሳታፊ
እንዲሆኑ ኃላፊነት ጥሎባቸዋል፡፡
የፕሮቶኮሉ ፈራሚ ሀገራት መብቶችን የማስጠበቅ፣ የመጠበቅ፣ የማሟላት ኃላፊነት እንዳለባቸው ሲያስቀምጥ ይህንንም
ለመተግበር ሕጎችን በማውጣትና በማሻሻል፣ ተቋማትን በማቋቋም ለተግባራዊነታቸው መሥራት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡
ኢትዮጵያም የአፍሪካ ሕዝቦች እና ሰዎች መብቶች ቻርተር የአፍሪካ አረጋውያን ፕሮቶኮልን በአዋጅ ቁጥር 1182/2012
በማጽደቅ የማስፈጸም ኃላፊነቱን ለሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመስጠት የሀገሪቱ ሕግ አካል ማድረጓን የኢፌዴሪ
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m