ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች።

0
42

መጋቢት 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስተኛ መደበኛ ጉባዔው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የስምንት ወራት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
ለምክር ቤቱ የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ገብረመስቀል ጫላ፤ ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።
በተጠቀሰው ወራት ከዘርፉ 2 ነጥብ 77 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር አስታውሰው፤ ከእቅዱ 91 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
ከግብርናው 1 ነጥብ 75 ቢሊዮን፣ ከኢንዱስትሪ ዘርፉ 320 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር፣ ከማዕድን ዘርፍ 389 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ተጨምረውበት በድምሩ 2 ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።
በዘንድሮው በጀት ዓመት ስምንት ወራት የተገኘው ገቢ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወራት ከተገኘው 2 ነጥብ 10 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/