ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ከቻይና ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲግ በጋራ በለሚ ከተማ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ ያሉ ሦስት ፋብሪካዎችን ወደ አምስት በመጨመር በኢንዱስትሪ ፓርክነት ለማሳደግ ከስምምነት ደረሰ።

0
209

የካቲት 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ከቻይና ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲግ በጋራ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ለሚ ከተማ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ ያሉ ሦስት ፋብሪካዎችን ወደ አምስት በመጨመር በኢንዱስትሪ ፓርክነት ለማሳደግ ከስምምነት ደረሰ።

የኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ ዋና ሊቀመንበር ዶክተር ብዙዓለም ታደለ በመልዕክታቸው በለሚ ከተማ እና በድሬዳዋ ከተማ ከዚህ በፊት የተጀመሩ ሦስት ፕሮጀክቶችን ወደ አምስት ፕሮጀክቶች በማሸጋገር ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክነት እንዲቀየር ለማድረግ የተደረገዉ ስምምነት ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታል ብለዋል።

ይህ ስምምነትም ሀገሪቱ በኢንዱስትሪ ዘርፍ አመርቂ ውጤት በማምጣት ከተሻሉ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ድርሻ ይኖረዋል ሲሉም ገልጸዋል።

በሲሚንቶ ምርቶች ላይ በጋራ ሲሠሩ የነበሩት ተቋማት በኹለቱ ከተሞች ያሉትን ፕሮጀክቶች ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክነት ለማሳደግ መስማማታቸዉ ሀገራዊ ስኬት መሆኑም ተጠቅሷል።

እስካኹንም ሲሚንቶ እና ጅፕሰም የሚያመርቱ ፕሮጀክት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

የአማራ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለፕሮጀክቱ መስፋፋት ላደረጉት ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል።

አኹን ላይ ተግባራዊ ለሚደረጉት አምስት ፕሮጀክቶች አጠቃላይ 600 ሚለየን ዶላር በጀት ተመድቧል ነው የተባለው።

ሁለቱ ኩባንያዎች በኢትዮጽያ በጋራ ለሚያከናውኑት ፕሮጀክት ደግሞ 2 ቢሊየን ዶላር ወጭ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ዘጋቢ:- ኤልሳ ጉዑሽ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/