አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በሩሲያ ፖርላማ የአፍሪካ ሀገራትና የሩሲያ ምክር ቤት የትብብር ኀላፊን ተቀብለው አነጋገሩ።

156
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ
ባሕር ዳር፡ ጥር 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዲሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በሩሲያ ፖርላማ የአፍሪካ ሀገራት እና የሩሲያ ምክር ቤት የትብብር ኀላፊ ኒኮላይ ኖቪችኮቭን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለው ግንኙነት አሁናዊ ሳይሆን ረጅም ዘመንን በጥንካሬ መጓዝ የቻለ ነው ያሉት ኒኮላይ ኖቪችኮቭን፤ ሩሲያ የኢትዮጵያን ሀገራዊ አንድነት ለመደገፍ ከኢትዮጵያ ጎን የምትቆምና ናት ብለዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎችን ሩሲያ በቅርበት የምትከታተል መሆኑን ገልፀው፣ ኢትዮጵያ ለብዙ ሀገራት ምሳሌ በሚሆን መልኩ የሰሜን ኢትዮጵያን ችግር በአፍሪካ ጥላ ስር መፍታቷ የሚደነቅ ተግባር ነው ብለዋል፡፡
አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው፤ ሩሲያ ለኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች እያደረገች ያለውን አዎንታዊ ድጋፍ አድንቀው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት ከምንጊዜውም በላይ መጠናከሩን ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የሰላም ጉዳይ ከፍተኛ መሻሻል እየታየበት እንደሆነ አንሰተዋል፡፡
በተለይም በጦርነቱ የነበረውን ችግር ለመፍታት አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች የሚለውን መርህ አድርጋ ተጠቅማበታለች ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በሁሉም አካባቢዎች ያለእረፍት ሰፋፊ ሥራዎችን እያከወነ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
ለሩሲያም ሆነ ለሌሎች ሀገራት ኢንቨስትሮች ምቹ ኹኔታን የሚፈጥር በመሆኑ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ የሩሲያ ባለሀብቶች በስፋት እንዲሳተፉ አፅንኦት ሰጥተው ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር በኩል ለአፈጉባኤ የተላከውን በአፍሪካና ሩሲያ ምክር ቤቶች ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ የተላከውን የግብዣ ደብዳቤ ዋናውን ከፒ ኒኮላይ ለአፈጉባኤ አስረክበዋል፡፡
የኢትዮጵያ በዚህ መድረክ ላይ መሳተፍም አህጉራዊ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ለተደረገለቸው ጥሪ የሩሲያ መንግሥትንና ሕዝብ አመስገነው፤ በሩሲያ የፌዴሬሽን ካውንስልና በፌዴሬሽን ምክር ቤት መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥለል ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!