“አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ ባወጀው ጦርነት ዜጎች ተፈናቅለዋል” አትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል

0
175

“አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ ባወጀው ጦርነት ዜጎች ተፈናቅለዋል” አትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል

ባሕር ዳር:ሐምሌ 26/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ገደማ ኢትዮጵያን በአስከፊ የመንግሥት ሥርዓት ውስጥ ሲጨቁን የነበረው አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ የተለያዩ ችግሮችን መፍጠሩን በአትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር ብሮንዊን ብሩተን ገለጹ፡፡

ምክትል ዳይሩክተሯ በትግራይ ለተፈጠረው የሰብዓዊ ድጋፍ ቀውስ ምክንያቱ የአሸባሪው ቡድን ነው ብለዋል፡፡

ምክትል ዳይሬክተሯ ብሮንዊን ብሩተን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጀውን የተናጠል ተኩስ አቁም ስምምነት አሸባሪው ቡድን አለመቀበሉ በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲስተጓጎል አድርጓል፡፡

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ላለፉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ሀገራዊ ለውጥ ወደጎን በመተው ለጦርነት እና ግጭት ሲዘጋጅ ቆይቷል ያሉት ብሮንዊን ብሩተን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት የዝግጅት ምዕራፉ ማጠናቀቂያ ነበር ብለዋል፡፡

እንደ ምክትል ዳይሬክተሯ ገለጻ መንግሥት ላለፉት ስምንት ወራት በትግራይ የነበረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ አቁሞ በሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ውሳኔ ቢያውጅም በአሸባሪው ቡድን ተቀባይነትን አላገኘም፡፡ መንግሥት የመከላከያ ኀይሉን ከትግራይ ክልል ካስወጣ በኋላም “አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ ባወጀው ጦርነት ተጨማሪ ዜጎች ተፈናቅለዋል” ነው ያሉት፡፡

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ለድጋሜ ጦርነት ራሱን በማዘጋጀት እና ትንኮሳ በመፈጸም ዳግም ወደአዲስ አበባ ለመምጣት ጥረት እያደረገ ይገኛል ያሉት የአትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል ምክትል ዳይሬክተሯ መንግሥት ሳይወድ በግድ ሕግ ወደማስከበር ዘመቻ መግባቱን ጠቁመዋል፡፡

በታዘብ አራጋው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m