አሸባሪው ትህነግ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ህጻናትን እሰከ መድፈር የደረሰ መሆኑን ከራያ ቆቦ የተፈናቀሉ እናት ተናገሩ፡፡

0
75
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪዉ የትህነግ ቡድን ባደረገዉ ወረራ ከራያ ቆቦ እና አካባቢዋ በርካታ ዜጎች ተፈናቅለዉ በደሴ ከተማ በተዘጋጁ ጊዚያዊ ማቆያዎች ዉስጥ ተጠልለዋል፡፡ ከሞቀ ጎጁአቸዉ የተፈናቀሉት ወገኖች ለእንግልት እና ስቃይ መዳረጋቸውን ይናገራሉ፡፡
አሸባሪዉ የትህነግ ቡድን ባደረገዉ ወረራ በራያ ቆቦ እና አካባቢዋ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙ ተፈናቃኞች ተናግረዋል፡፡ ወይዘሮ ትዕግስት አለዉ የአንድ ዓመት ልጇን ይዛ በዝናብ እና በብርድ የ3 ቀን የእግር ጉዞ ተጉዛ ህይወቷን ማትረፍ ችላለች፡፡ የአሸባሪ ቡድኑን ጭካኔ ለመግለፅ ከባድ መሆኑን የምታስረዳዉ ትዕግስት በቅርብ የምታዉቃት የ11 ዓመት ታዳጊ ህጻን በጁንታዉ ታጣቂዎች ተደፍራለች፡፡
በራያ ቆቦ እና አካባቢዋ የንብረት ዘረፋ እና ዉድመት እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል፡፡ ወይዘሮ ትዕግስት ባለቤቷ ከእሷ ዘግይቶ በመውጣቱ በጁንታዉ ታጣቂዎች ተይዞ ከባድ ድብደባ ተፈጽሞበታል፡፡
የያዛቸው ንብረቶችም በአሽባሪ ቡድኑ መወሰዳቸውን ተናግራለች፡፡ የአንድ አመት ህፃን ልጇን ይዛ ጋራ ሽንተረሩን በዝናብ እያቆራረጠች የ3 ቀን የእግር ጉዞ የተጓዘችዉ ወይዘሮ ትዕግስት አሸባሪዉ ቡድን ያደረሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሥነ ልቦና ችግር እንደዳረጋት ነው የነገረችን፡፡
ዘጋቢ፡- አንዋር አባቢ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ