አሸባሪው ትህነግ በአማራና በአፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ የሀገሪቱን አንድነትና ሉዓላዊነት የማስጠበቅ የሞራል፣ የሕግና የፖለቲካ ግዴታ ያለበት የፌዴራል መንግሥት የመከላከል አቅሙን ለመጠቀም እንደሚገደድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

0
211

አሸባሪው ትህነግ በአማራና በአፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ የሀገሪቱን አንድነትና ሉዓላዊነት የማስጠበቅ የሞራል፣ የሕግና የፖለቲካ ግዴታ ያለበት የፌዴራል መንግሥት የመከላከል አቅሙን ለመጠቀም እንደሚገደድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔው አሸባሪው ትህነግ እየፈጸመ ባለው ወረራ ዓላማውን ሊያሳካ እንዳልቻለ አስታውቋል።

አሸባሪው ቡድን በአማራና በአፋር ክልሎች በከፈተው ወረራ በክልሎቹ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች እንዲፈናቀሉ አድርጓል ነው ያለው ሚኒስቴሩ።

መንግሥት የተኩስ አቁም ውሳኔውን ለማክበር ጥረት እንዳደረገ የገለጸው ሚኒስቴሩ አሸባሪው ቡድን ግን እየፈጸመ ያለውን ሰብዓዊ ግፍ ቀጥሎበታል ብሏል። በመሆኑም መንግሥት በአሸባሪው ትህነግ ተጨማሪ ጥፋትና ግፍ እንዲፈጸምና ዜጎች ኑሯቸው እንዲመሰቃቀል የማይፈቅድ መሆኑን ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስገንዝቧል።

መግለጫው የአሸባሪው ቡድን ሀገር የማፍረስ የሽብር ድርጊት የመንግሥትን ትዕግስት በመፈታተን የተኩስ አቁም የውሳኔ ሃሳብን ለመለወጥ እንደሚያስገድድም አመላክቷል።

ሰላም እንዲሰፍን በመንግሥት በኩል ሰፊ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ያስታወሰው ሚኒስቴሩ፤ አሸባሪው ትህነግ በትግራይ ክልል እያደረሰ ያለውን የሽብር ተግባር ወደ አጎራባች ክልሎች በማስፋት ሰብዓዊ ቀውስ እያደረሰ መሆኑን አስገንዝቧል።

የመንግሥትን የተናጠል የተኩስ አቁም በመጣስ በዜጎች ላይ ግፍ እየፈጸመ የሚገኘውን አሸባሪ ቡድን የዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ከዝምታና ተገቢ ካልሆነ እይታ ወጥቶ ሊያወግዝ እንደሚገባ ሚኒስቴሩ ጠይቋል።

አሸባሪ ቡድኑ በአማራና በአፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ የሰላም አማራጭ እንዲዘጋ እያደረገ መሆኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ የሀገሪቱን አንድነትና ሉዓላዊነት የማስጠበቅ የሞራል፣ የሕግና የፖለቲካ ግዴታ ያለበት የፌዴራል መንግሥት የመከላከል አቅሙን ለመጠቀም እንደሚገደድም አስገንዝቧል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here