አሸባሪው ትህነግ በመንግሥት የተላለፈውን የተናጠል የሰብዓዊ የተኩስ አቁም ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ስደተኞች በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ሳይቀር አዳዲስ ጥቃቶችን መክፈቱን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

164

አሸባሪው ትህነግ በመንግሥት የተላለፈውን የተናጠል የሰብዓዊ የተኩስ አቁም ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ስደተኞች በሰፈሩባቸው
አካባቢዎች ሳይቀር አዳዲስ ጥቃቶችን መክፈቱን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 07/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ እንደገለጸው፤ አሸባሪው ትህነግ
የመንግሥትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ውድቅ አድርጎ ስደተኞች ላይ ጥቃት እየፈጸመ ነው። በዚህ የአሸባሪው ትህነግ
ጥቃት ምክንያት በማይ-ዓይኒ እና በአዲ-ሐሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙት ኤርትራዊያን ስደተኞች ደኅንነታቸው ላይ አደጋ ላይ
እንደወደቀ ኤጀንሲው አስታውቋል።
ስደተኞቹ ደኅንነታቸው ሊጠበቅ ወደሚችልባቸው አካባቢዎች እንዲዛወሩ፣ በድጋፍ ላይ የተመሠረተ የከተማ ስደተኝነት እውቅና
እንዲሰጣቸው እና ወደ ሦስተኛ ሀገር እንዲዛወሩ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ብሏል፡፡
በችግሩ ዙሪያ ከስደተኞች ተወካዮች ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ማካሄዱን የገለጸው ኤጀንሲው፤ በሐምሌ 06/2013 ዓ.ም
በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽነር የኢትዮጵያ ተወካይ በተገኙበት በመመስረት ላይ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ
በሚገኝበት ዓለም-ዋጭ በመገኘት ከስደተኛ ተወካዮች ጋር ውይይት ተደርጓል ብሏል፡፡
“መንግሥት የስደተኞች ድምጽ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ይደመጣል በሚል ተስፋ በአዲስ መጠለያ ጣቢያ ለማስፈር እና
በድጋፍ ላይ የተመሠረተ የከተማ ስደተኝነት እውቅና ለመስጠት ጠንክሮ እየሠራ ይገኛል” ነው ያለው፡፡
በመንግሥት በኩል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን እና ለውጦችን በመረዳት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ውጤታማ እና ተጨባጭ
ድጋፎችን በማድረግ ስደተኞችን በአዲስ መጠለያ ጣቢያ የማስፈሩን ሂደት ለማፋጠን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ
እናቀርባለን ሲልም ኤጀንሲው በመግለጫው ማስታወቁን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m