አሸባሪው ቡድን ከውጭ አካላት ጋር በመመሳጠር ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ለማድረስ ሐሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጨ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎች መገናኛ ብዙኀን ኀላፊ ቢለኔ ስዩም ገለጹ፡፡

0
90

አሸባሪው ቡድን ከውጭ አካላት ጋር በመመሳጠር ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ለማድረስ ሐሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጨ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎች መገናኛ ብዙኀን ኀላፊ ቢለኔ ስዩም ገለጹ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎች መገናኛ ብዙኀን ኀላፊ ቢለኔ ስዩም ለውጭ እና ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም መንግሥት በትግራይ ክልል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብዓዊ ድጋፎች ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲደርሱ ጥረት ቢያደርግም አሸባሪው ትህነግ የመንግሥትን የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ በመጣስ የሰብዓዊ ድጋፉን እያስተጓጎለ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

አንዳንድ መገናኛ ብዙኀን የተሳሳተና የተዛባ ዘገባ በማቅረብ የሚፈጠሩ ሁሉንም ችግሮች ለመንግሥት የመስጠትና መንግሥትን ተጠያቂ በማድረግ ተግባር ላይ መሰማራታቸውንም ኀላፊዋ ገልጸዋል።

አሸባሪው ትህነግ ከውጭም ከውስጥም ባለው ትስስር ሐሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጨ እንደሚገኝ አመልክተው “የሚሰራጨው የተሳሳተ መረጃና በዜጎች ላይ የሽብር ቡድኑ የሚያካሂደውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ቀስ በቀስ መረዳቱ አይቀርም” ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ የሰብዓዊ ድጋፎችን ለመደናቀፍ ወደ አጎራባች አፋርና አማራ ክልሎች ወረራ በመፈጸም ዜጎች እንዲፈናቀሉ ማድረጉንም ነው የገለጹት።

አሸባሪው ቡድን ከውጭ አካላት ጋር በመመሳጠር ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ለማድረስ ሐሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጨ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

አሸባሪው ትህነግ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨትም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ የኢትዮጵያን ሁኔታ በተመለከተ የተዛባ ገጽታ በመገንባት ላይ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

“መንግሥት በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ወደ ሕግ ማስከበር ዘመቻ ተግባር መግባቱን አሁንም ቢሆን አንዳንድ አካላት ማየት አልፈለጉም” ነው ያሉት። በሕግ ማስከበሩ ዘመቻው ወቅት ክልሉን መልሶ ለማቋቋም መንግሥት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ማውጣቱንም አስታውሰዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here