“አሸባሪው ሕወሓት በሕጻናት ህይወት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተውተረተረ ይገኛል” መከላከያ ሚኒስቴር

0
148

“አሸባሪው ሕወሓት በሕጻናት ህይወት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተውተረተረ ይገኛል” መከላከያ ሚኒስቴር

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) “አሸባሪው ሕወሓት በሕጻናት ህይወት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተውተረተረ ነው” ሲል መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ባለፉት ሁለት ቀናት በአፋር ክልል አለሌ ሱሉላ አካባቢና በአማራ ክልል በራያ ቆቦ ለትንኮሳ የመጣው አሸባሪ ቡድን ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል።

አሸባሪው ሕወሓት ሕጻናትን እያስገደደ ለሦስት ቀናት ያልበለጠ ሥልጠና በመስጠት ወደ ውጊያ አስገብቶ መቋቋም በማይችሉት ጦርነት እየማገዳቸው መሆኑን ነው መከላከያ ሚኒስቴር የገለጸው።

“በጦር ሜዳ ካሰለፋቸው ሕጻናት ድል አገኛለሁ ብሎ በማሰብ እያስጨረሳቸው ይገኛል” ያለው ሚኒስቴሩ፤ ይህ ሳይበቃ በውጊያ የተገደሉትን ሕጻናት አስክሬን በመሰብሰብ “የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት ገደላቸው” ብሎ በውጊያ ያስጨረሳቸውን ሕጻናት ሬሳ መነገጃ ለማድረግ የተለመደውን የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ሬሳቸውን ኹሓ ላይ ሰብስቦ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ አሳልፎ ከትግራይ መውጣቱን ካሳወቀ በኋላ የአሸባሪው ቡድን ሠራዊቱን እየተከተለና እየተነኮሰ እርሱ በፈጠረው ውጊያ የተመታ እንጂ ሠራዊቱ የራሱን የማጥቃት እርምጃ አልወሰደም ነው ያለው የመከላከያ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m