”አሸባሪው ህወሓት ቀድሞም ህጻናትንና አረጋውያንን በጦር ግንባር የማሰለፍ አሳፋሪ ልምድ ያለው ቡድን ነው” ሜጀር ጄነራል መርዳሳ ሌሊሳ (አባ መላ)

0
122

”አሸባሪው ህወሓት ቀድሞም ህጻናትንና አረጋውያንን በጦር ግንባር የማሰለፍ አሳፋሪ ልምድ ያለው ቡድን ነው” ሜጀር ጄነራል መርዳሳ ሌሊሳ (አባ መላ)

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ህወሓት ቀድሞም በትጥቅ ትግል ወቅት ህጻናትንና አረጋውያንን በጦር ግንባር የማሰለፍ አሳፋሪ ልምድ ያለው ቡድን እንደሆነ የቀድሞው 18ኛው ተራራ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል መርዳሳ ሌሊሳ (አባ መላ) አስታወቁ።

ሜጀር ጄነራል መርዳሳ ሌሊሳ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የአሸባሪው ህወሓት አመራሮች በትጥቅ ትግል ወቅትም ህጻናትን እና አረጋውያንን በጦርነት በማሰለፍ ጥይት ለማብረጃነት ሲጠቀሙ ነበር። አሁንም በጠብ አጫሪነታቸው የትግራይን ሕዝብ ለእልቂት እየዳረጉ የሚገኙ አጥፊዎች ናቸው።

ቡድኑ ቤተክርስቲያን እና ገበያ ውስጥ ጦርነት በመክፈት ህዝብን የማስጨረስ የቆየ ልምድ ያለው ነው። አሁንም በህዝብ ደም ለመንገስ በማለም መሳሪያ ማንገብ የማይችሉ እናቶችንና ወደትምህርት ቤት መሄድ የነበረባቸውን ህጻናት በውጊያ በማሰለፍ እድሜውን ለማራዘም እየተፍጨረጨረ ነው ብለዋል።

የአሸባሪው ቡድን ሕዝብን ከፊት አድርጎ ለጥቃት የመነሳሳት እኩይ ተግባር ቀድሞም የነበረ መሆኑን እማኝ መሆናቸውን የሚናገሩት ሜጀር ጄነራል መርዳሳ፤ አሸባሪው ቡድን በትጥቅ ትግሉ ወቅት በ1968 ነሐሴ 16 ቀን ሽሬ ከተማ ዙሪያ በምትገኝ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በርካታ ሴቶችና ህጻናት እንዲሁም አረጋውያን በተሰበሰቡበት የገበሬ ልብስ ለብሰው የደፈጣ ተኩስ መክፈቱን አስታውሰዋል።

የቡድኑ አባላት ጋቢ እና ነጠላ በመልበስ ጸሎተኛ በመምሰል ከህዝቡ ጋር ተቀላቅለው ተኩስ ሲከፍቱ በአጠገባቸው በርካታ ህጻናት ነበሩ። በወቅቱ የኢትዮጵያ ጦር ህዝብን ላለመጉዳት ሲል አፈግፍጎ ነበር የተከላከላቸው ብለዋል። ነብሰጡር ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን ለውጊያ እንደሚጠቀሙ አስታውቀዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here