አሸባሪው ህወሃት በጦርነት ያስጨረሳቸውን ህጻናት አስከሬን በመንግሥት በጅምላ የተፈፀመ ግድያ ለማስመሰል እየተፍጨረጨረ ነው።

0
283

አሸባሪው ህወሃት በጦርነት ያስጨረሳቸውን ህጻናት አስከሬን በመንግሥት በጅምላ የተፈፀመ ግድያ ለማስመሰል እየተፍጨረጨረ ነው።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ህወሃት በሀሺሽ አስክሮ በጦርነት ያሰጨረሳቸውን ህጻናት አስከሬን በመንግሥት በጅምላ የተፈፀመ ግድያ ለማስመሰል እየጣረ መሆኑን ምንጮቹን ጠቅሶ ኢፕድ አስታውቋል።

አሸባሪው ህወሃት በአውደ ውጊያው ያጣውን ድል በቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ ለማግኘት እየተፍጨረጨረ ነው።

በተለይ ሰሞኑን የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሳማንታ ፓዎር ወደ “ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው” የሚለው ዜና ከተሰማ በኋላ የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳውን በመንዛት መንግሥትን ለመክሰስ እየሞከረ መሆኑንና የሽብር ቡድኑ የህጻናትን አስከሬን በመንግሥት የተገደሉ አስመስሎ ለማቅረብ እየሞከረ ነው።

የመከላከያ ሠራዊት ከመቀሌ ከወጣ በኋላ አሸባሪው ህወሃት በክልሉ በእምነታቸው፣ በፖለቲካ አቅማቸው ሰዎችን እየገደለ መሆኑንም ገልጸዋል።

በተለይ ቡድኑ የትግራይ ተወላጆችን “የጊዜያዊ አስተዳደር አባላት ናችሁ” እንዲሁም “የመከላከያ ሠራዊቱን ቀልባችኋል” እና ሌሎች ምክንያቶችን በመደርደር የክልሉን ተወላጆች እየገደለ መሆኑን ጋዜጠኛ አርዓያ ተስፋማርያም ከኢዜአ ጋር ባደረገው ቆይታ አጋልጧል።

ቡድኑ እስከቅርብ ቀናት ድረስ ከ450 በላይ ንጹሃንን የገደለ ሲሆን፤ በውቅሮ፣ በአክሱምና በሌሎች አካባቢዎች በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ያተኮረ ጥቃት መሰንዘሩንም ነው ጋዜጠኛው ያሳወቀው።

በሌላ በኩል የሽብር ቡድኑ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህጻናትን በማስገደድና ከሶስት ቀናት ያልበለጠ ስልጠና በመስጠት ለጦርነት ሲያሰማራ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቻችን፤ በአሁኑ ወቅት የደረሰበትን ከባድ ሽንፈትና ኪሳራ ለመሸፈን ፍጹም ከሰብዓዊነት በወጣ መልኩ የህጻናቱን አስከሬን መንግሥት እንደጨፈጨፋቸው ለማስመሰል መቀሌ ላይ ማከማቸቱን ጠቅሰዋል።

የህጻናቱን አስከሬን በማሰባሰብ “የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት ገደላቸው” ብሎ በውጊያ ያስጨረሳቸውን ህጻናት መነገጃ ለማድረግ የተለመደውን የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ ለማሰራጨት ጥረት እያደረገ መሆኑንም ምንጮቹ አረጋግጠማል።

መንግሥት የትግራይ ሕዝብ የመኸር እርሻ ተረጋግቶ እንዲያከናውንና በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ የተናጥል ተኩስ አቁም ተግባራዊ ማድረጉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም አሸባሪው የህወሃት ቡድን ህጻናትን በሀሺሽ በማስከር ወደ ጦርነት በማሰማራት በትግራይ አጎራባች ክልሎች ላይ ጥቃትና ዘረፋ እየፈጸመ ይገኛል።

አሸባሪ ቡድኑ በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የጋረጠውን አደጋ ለመመከት ኢትዮጵያውያን እየሰሩ ሲሆን፤ ከዚህ አኳያ የሽብር ቡድኑ ህጻናትንና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ሳይቀር ወደ ጦርነት በማሰማራት አረመኔያዊ ድርጊት እየፈጸመ እንደሚገኝ መዘገቡ ይታወሳል።

የሽብር ቡድኑ ይህ አልበቃ ብሎት በሀሺሽ እያሰከረ በጦርነት በአሰማራቸው ህጻናት ህይወት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተውተረተረ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ህወሃት በህጻናት ህይወት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየጣረና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸ ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታን መምረጡ ብዙዎችን አሰገርሟል።

የመከላከያ ሠራዊት ከመቀሌ ከወጣ በኋላ አሽባሪው ህወሃት በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመው ግፍ ከዕለት ተዕለት እጅግ እየከፋ መምጣቱን መዘገቡ ይታወሳል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here