አሸባሪውን ትህነግ በተባበረ ክንድ ላይመለስ መቅበር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

0
72

አሸባሪውን ትህነግ በተባበረ ክንድ ላይመለስ መቅበር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጀግናውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልን እና ሚሊሻ የሚደግፍ እና ሽብርተኛውን ትህነግ የሚያወግዝ ሰልፍ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው።

የድጋፍ ሰልፉ ተሣታፊዎች በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ አሸባሪውን ትህነግ ላይመለስ በተባበረ ክንድ መቅበር እንደሚገባ ገልጸዋል።

በሰልፉ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሞላ መልካሙ የህልውና ዘመቻው የአማራን ሕዝብ የመታደግና የኢትዮጵያን ሀገረ መንግሥት የማፅናት ተልዕኮ ነው ብለዋል።

አሸባሪው ትህነግ የአማራን ሕዝብ በቀዳሚ ጠላትነት ፈርጆ እና ፀረ ኢትዮጵያ ኾሆ መቆየቱ በታሪክ የተመዘገበ ብቻ ሳይሆን ባለፉት 27 ዓመታት ሲፈፅመው የኖረው ተግባሩ መሆኑን አንስተዋል።

ከንቲባው የድርድር አማራጮችን ገፍቶ ሽፍታ የሆነው አሸባሪው ትህነግ በአማራና በአፋር ክልሎች በከፈተው ጦርነት መቀበሪያው ይሆናል ብለዋል፡፡ ሕዝቡ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለልዩ ኃይሉ እና ለሚሊሻው ደጀን በመሆን ትግሉን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

አሸባሪው ትህነግ ሕፃናትን ለጦርነት እየማገደ መሆኑን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊረዳው እንደሚገባ ሰልፈኞቹ መልእክት አስተላልፈዋል። የውጭ ኃይሎች እጃቸውን እንዲሰበስቡም ነው የጠየቁት።

ዘጋቢ፡- አገኘሁ አበባው-ጎንደር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here