አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ ዝግጅት ማድረጋቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

0
238

አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ ዝግጅት ማድረጋቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ ወረራ ካካሄደባቸው አካባቢዎች ሰሜን ጎንደር ዞን አንዱ ነው። በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ ዝግጅት ተጠናቅቋል።

አሚኮ ያነጋገራቸው የደባርቅ ከተማ ነዋሪ አቶ ነጋ ተገኜ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት መሠረታዊ የውትድርና ስልጠና በመውሰድ ግንባር ለመሠለፍ ዝግጅት አድርገዋል። ግንባር መዝመት የማይችሉ ደግሞ ለጸጥታው ኃይል ስንቅ እንዲያዘጋጁና አካባቢውን በንቃት እንዲጠበቁ መደረጉን ተናግረዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ነዋሪዎች በርካታ የአሸባሪው ሰርጎ ገቦችን በመያዝ ተገቢ ቅጣት እንዲያገኙ እያደረጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ሌላዋ የከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ሰላማዊት ወርቄ ሴቶች ከጸጥታ ኀይሉ ጋር በመቀናጀት ጠላትን ድባቅ ለመምታት ተዘጋጅተናል ነው ያሉት። በአሁኑ ወቅት የሌሊት ጥበቃ እያደረጉ መሆናቸውን የገለጹት ወይዘሮ ወርቄ ወደ ግንባር በመዝመት ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከልዩ ኃይልና ከአማራ ፋኖ ጎን ለመሠለፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ ላይ መሆናቸውንም ነግረውናል።

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አየልኝ ገበየሁ ነዋሪዎች አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ በቂ ዝግጅት አድርገዋል ነው ያሉት። ወጣቶች ከምንጊዜውም በላይ ከጸጥታ ኀይሉ ጎን ተሠልፈው የሚያደርጉት ርብርብ ምስጋና የሚቸረው ነው ብለዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የሦስተኛ ዙር ስልጠና በመስጠት ሚሊሻው ወደ ግንባር ተሠማርቷል ብለዋል።

ዘጋቢ ፦ አዳሙ ሽባባው – ከደባርቅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here