“አሸባሪውን ቡድን በቅርቡ ግብዓተ መሬቱ ይፈፀማል” ሴት የመከላከያ የሠራዊት አባላት

0
352

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሴት የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የአሸባሪ ቡድኑን ግብዓተ መሬት ካልፈፀመን አንመለስም፤ ይህም በቅርቡ ይሆናል ብለዋል፡፡

የደቡብ እዝ ሴት የሠራዊት አባላት ጠላትን በመደምሰስ ላይ ይገኛሉ፡፡

አስር አለቃ ሰላማዊት ኀይሉ በግንባር ካገኘናቸዉ ሴት የመከላካያ ሠራዊት አባላት መካከል አንዷ ናት፡፡ ጀግንነት የአባቶቻችን ነዉ የምትለዉ አስር አለቃ ሰላማዊት ጠላትን ለመደምሰስ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ሠራዊቱ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግራለች፡፡

ይህን ዘራፊ እና አሸባሪ ብድን ግብዓተ መሬት ፈፀመን ነዉ የምንመለሰዉ ብላለች፡፡

ሌላኛዋ ከመከላካያ ሠራዊት አባላት መካከል አንዷ የሆነችዉ ሀምሳ አለቃ ትዕግስት ሽመልሽ ሴት የሠራዊት አባላቱ በጠላት ላይ ጀብድ እፈፀሙ መሆናቸዉን ተናግራለች፡፡

ሴት የሠራዊት አባላቱ ከወንድ ጓዶች ጋር በመቀናጀት እንቢ ለሀገሬ ብለዉ ይህን ወራሪ እና አሸባሪ ቡድን እስከወዲያኛዉ ለመሸኘት በሚደረገዉ የትግል ሂደት ዉስጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረጉ መሆናቸዉን ገልፃለች፡፡

ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረገችዉ አስር አለቃ አዱኛ ጀማል ደግሞ ጠላት እየተደመሰሰ ነው፤ በቅርቡ ግብዓተ መሬቱ ይፈፀማል ብላለች፡፡

የሀገር መከላካያ ሠራዊቱ እንኳን ይህንን የባንዳ ስብስብ ቡድን ይቅርና የዉጭ ጠላትን ያንበረክካል ያለቸዉ አስር አለቃ አዱኛ ሕዝቡ በሐሰት መረጃ ሳይደናገር ከሠራዊቱ ጎን እንዲቆም ጠይቃለች፡፡

ዘጋቢ:— አንዋር አባቢ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m