አርሶ አደሮች የካሳ ክፍያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት የሚያደርግ ተቋም ለማዋቀር እየተሠራ መኾኑን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ተናገሩ።

58
ባሕር ዳር:መጋቢት 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አርሶ አደሮች የካሳ ክፍያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት የሚያደርግ ተቋም ለማዋቀር እየተሠራ መኾኑን ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ተናግረዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ የምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሠጡ ነው። የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በካሳ ክፍያ ተጠቃሚ መኾን እንደሚገባቸውም ተናግረዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ የከተማ ልማት እና የአርሶ አደሮችን የካሳ ክፍያ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ አርሶ አደሮች በካሳ ክፍያ እንዳይጎዱ ማድረግ ይገባል ብለዋል። አርሶ አደሮች የካሳ ክፍያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት የሚያደርግ ተቋም ለማዋቀር እየተሠራ መኾኑንም አንስተዋል። በልማት ስም የሚነሱ አርሶ አደሮች ተጎጂ መኾን የለባቸውም ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ።
የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን በዘላቂነት ማቋቋም በቀጣይ ለሚካሄዱ የከተማ ልማት ሥራዎች መሬት ሲፈለግ በቀላሉ በተግባቦት ለመፈጸም ያግዛል ነው ያሉት። አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ ካልተቻለ ከተሞችን ማስፋፋት እና ገጠር እና ከተማን ማስተሳሰር እንደማይቻልም ገልጸዋል።
በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት በሪል ስቴት አማካኝነት ቤቶችን ገንብቶ ለማቅረብ እንደሚሠራም ተናግረዋል። በተለይም በትልልቅ ከተሞች ላይ ቤቶችን ወደ ላይ ፎቆች አድርጎ የማሠራት ሥራ ይሠራል ነው ያሉት። የዞን እና የወረዳ ይከፈልልን ጥያቄዎች በጥናት እንደሚመለሱም ገልጸዋል።።
ዘጋቢ: ታርቆ ክንዴ