“አምባሳደሮች የተሰጣቸውን ተልዕኮ የሚመጥን ሥራ አሟልተው መሥራት አለባቸው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

0
83

የካቲት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አምባሳደሮች የተሰጣቸውን ብሔራዊ ተልዕኮ የሚመጥን ሥራ አሟልተው መፈጸም እንዳለባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰበዋል። አቶ ደመቀ ይህን ያሉት በቅርብ ለተሾሙ አምባሳደሮች እየተሰጣቸው ባለው ስልጠና ላይ በመገኘት ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ ሀገራት የሚሰማሩ አምባሳደሮች ተለዋዋጭ የኾነውን የዓለምን ፍላጎት ከግምት ባስገባ መልኩ በቂ ዝግጅት አድርገው ተልዕኳቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል። የሚሄዱበትን አካባቢም በደንብ በማወቅና በመቃኘት ለሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም መከበር በተለየ ትኩረት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ባለፈው አንድ ዓመት የኢትዮጽያን ሉዓላዊ ክብር የተዳፈሩ የዲፕሎማሲ ጫናዎች እንደነበሩ ያስታወሱት አቶ ደመቀ ያልተገቡ ጫናዎችን ኹሉ በሕዝብና ዳያስፖራው ጠንካራ ድጋፍ በፀጥታ ኃይሎች ተጋድሎና በመንግሥት ጠንካራ አቋም ተሻግረናቸዋል ብለዋል። በቀጣይም የሚገጥሙንን ፈተናዎች የሀገራት ተለዋዋጭ ፍላጎት እያስተዋሉ ጠንካራ ሥራ መሥራት እንደሚገባ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/