አምባሳደር ካሳ ከበደ (ዶ.ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

248

አምባሳደር ካሳ ከበደ (ዶ.ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ታኅሣሥ 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አምባሳደር ካሳ ከበደ (ዶ.ር) ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

አምባሳደር ካሳ ከበደ (ዶ.ር) በተለያዩ ኃላፊነቶች ሀገራቸውን ያገለገሉ አንጋፋ ዲፕሎማት ሲሆኑ በጄኔቫ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆንም አገልግለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት እና ሠራተኞቹ በአምባሳደሩ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸው እና ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation