አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳይ ምክትል ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ።

57
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አምባሳደሯ በኢትዮጵያ እና በኅብረቱ መካከል ያለውን ግንኙነት በአዲስ መልክ ማደስ በሚቻልበት ላይ መክረዋል።
በቤልጂየም፣ ሉክሰምበርግ እና የአውሮፓ ኅብረት ተቋማት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳይ ምክትል ዋና ጸሐፊ ኤነሪኬ ሞያ ጋር ውይይት አደረጉ።
የውይይታቸው ትኩረትም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በኅብረቱ መካከል ያለውን ግንኙነት በአዲስ መልክ ማደስ በሚቻልበት ላይ መክረዋል።
አምባሳደር ሂሩት ስለ ሽግግር ፍትሕ ማዕቀፍ፣ የሰላም ስምምነቱ አሁን ያለበትን ደረጃ እና የሀገራዊ ምክክር ዝግጅትን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳይ ምክትል ዋና ጸሐፊ ኤንሪኬ ሞራ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በቅርብ ለመከታተል ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
በሚቀጥለው ሳምንት በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በሀገሪቷ መሬት ያለውን እውነታ ለማወቅ እንደሚያግዛቸው መግለጻቸውን በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!