“አምስት ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ነጻ የትምህርት እድል ተጠቃሚ ሊያደርጉ ነው” ትምህርት ሚኒስቴር

24

ባሕር ዳር: ግንቦት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች የመክፈል አቅም የሌላቸው ተማረዎችን ነጻ የትምህርት እድል ተጠቃሚ ሊያደርጉ መኾኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል
ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶቹም ሊሴ ገ/ማርያም ፣ ጣሊያን ት/ቤት ፣ ቤንግሀም አካዳሚ ፣ ሳንፎርድአለም አቀፍ ት/ቤትና አሜሪካን ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ናቸው።

የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች ኀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የመማር አቀም እያላቸው ከፍለው መማር ያልቻሉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሀገራችን ያሉ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች 10 በመቶ ተማሪዎችን ተቀብለው እንዲያስተምሩ ከስምምነት ደርሰዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶቹ አቅም እያላቸው ከፍለው መማር ያልቻሉ ተማሪዎችን በራሳቸው ፍላጎት ተቀብለው እንደሚያስተማሩ ጠቁመው ለትምህርት ቤቶቹም ምሥጋና ማቅረባቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶቹ ርእሳነ መመህራንና ኀላፊዎች በበኩላቸው የየሀገራቸው የትምህርት ፖሊሲ ለሁሉም እኩል የትምህርት እድል እንደሚፈቅድ ጠቁመው የኢትዮጵያ ተማሪዎችንም ተጠቃሚዎች ለማድረግ ከሚኒስቴሩ ጋር በጋር እንደሚሠሩ አስታውቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!