አዲስ አበባ: ጥር 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ባንክ ማኀበረሰባዊ አገልግሎቱን ለማስፋት በዘንድሮው ዓመት በሀገር አቀፍ ፈተና በመላ ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በወር 750 ብር እየከፈለ እንደሚያስተምር አስታውቋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ ባንካችን ከባንክ ባሻገር ሲል በምክንያት ነው፤ ይህንም የማኅበረሰባዊ አገልግሎት በመስጠት እየተገበረ ይገኛል ብለዋል።
ዘጋቢ:- እንዳልካቸው አባቡ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!