አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና የአማራ ክልል በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ልማት ፈንድ ጽሕፈት ቤት በትብብር መሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

244

ባሕር ዳር: ነሐሤ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና የአማራ ክልል በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ልማት ፈንድ ጽሕፈት ቤት የወደሙ ተቋማትን ለመገንባትና ለማልማት የአምስት ዓመታት ቆይታ የተቋቋመ ሲኾን ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመሥራት ዛሬ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

የመግባቢያ ሰነዱንም የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥዬ እና የፈንድ ጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አባተ ጌታሁን (ዶ.ር) ናቸው የተፈራረሙት።

ዶክተር አባተ የፈንድ ጽሕፈት ቤቱ አምስት ሰዎችን ይዞ የተቋቋመ ሲኾን የተለያዩ ተቋማትን እና ድርጅቶችን በማስተባበር ሥራውን እንደሚያከናውን ገልጸዋል። ጽሕፈት ቤቱ የተሰጠውን ተልዕኮም በዝርዝር አብራርተዋል። ከተልዕኮዎቹ መካከልም:-

👉የወደሙ ተቋማትን ለመገንባት የሚውል ፋይናንስ በማፈላለግ አስቸኳይ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን መልሶ ማቋቋምና የሥራ እድል ፈጠራ ናቸው ብለዋል።

“በጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል በ20 ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ውስጥ 291 ቢሊዮን ብር ወድሟል” ያሉት ዶክተር አባተ ይኽንን ውድመት ለሕዝብ አሳውቆ ንቅናቄ የሚፈጥር የተግባቦት ሥራ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።

የወደሙ ተቋማትን ለሀገር ውስጥና ለውጭው ማኅበረሰብ ለማሳወቅና መልሶ በመገንባት ዙሪያ ሚዲያዎች የላቀ ሚና እንዳላቸው የጠቀሱት ዶክተር አባተ በተለይም የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተለመደውን ሙያዊ አበርክቶ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት።

አሚኮ እና ሌሎችም የሀገር ውስጥና የውጭ ተደራሽ ሚዲያዎች የወደሙ ተቋማትን ለመገንባት በሙያው ከመረባረብ ባለፈ የችግሩን ምንጭ ለማድረቅና ለዳግም ወረራ ላለመጋለጥ ሕዝቡን የማንቃትና ወደ ልማት ለማሰማራት መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ዶክተር አባተ የወደመውን ንብረት መተካት የሚቻለው በጋራ በመቆም ውጤታማ ሥራ ማከናወን ሲቻል በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መረባረብ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ሰጥዬ የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባትና በሕዝብ ላይ የደረሰውን ሁሉን አቀፍ ጉዳት ለመቀልበስ አሚኮ ባለሙያዎችን በሁሉም አካባቢ እያሰማራ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አሚኮ በ2015 በጀት ዓመት እቅዱ የወደሙ ተቋማት የሚገነቡበትን መንገድ በትኩረት እንደሚሠራ አቶ ሙሉቀን ጠቁመዋል።

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከአማራ ክልል በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ልማት ፈንድ ጽሕፈት ቤት ጋር በቅንጅት ለመሥራት ቁርጠኛ መኾኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ሙሉቀን አረጋግጠዋል።

የአማራ ክልል በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ልማት ፈንድ ጽሕፈት ቤት የወደሙ ተቋማትን ለመገንባትና ለማልማት የድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች

አማራ ባንክ 9900000965368
ዓባይ ባንክ 2012118144610010
ዳሽን ባንክ 0079333826011
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000486031003
አቢሲኒያ ባንክ 102245563
አዋሽ ባንክ 01304929559100
ቡና ባንክ 1079601001096 ናቸው።

ዘጋቢ:–አሜንአዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/