አመልድ ኢትዮጵያ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡

0
71

ባሕር ዳር ፡ ጥር 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞ አማራ መልሶ ማቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) የአሁኑ አመልድ ኢትዮጵያ ለ10 ዓመታት ያከናወናቸውን የልማት ሥራዎች፣ ለላቀ ተደራሽነት ድርጅቱ መጠሪያ ስያሜን የማስተዋወቅ እንዲሁም የ5 ዓመታት ስትራቴጂክ እቅዱን ከጠቅላላ የጉባዔው አባላት ጋር በባሕር ዳር እያስተዋወቀ ይገኛል።

በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) አመልድ በተከታታይ በልማትና በማኅበራዊ ሥራዎች ሕዝቡን በማሳተፍ የኅብረተሰቡን ችግር ሲፈታ ቆይቷል ብለዋል። ድርጅቱ በአማራ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ በተለይ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ ተግባራት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ተቋሙ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትንም አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡

አመልድ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብትን በማልማት፣ በአነስተኛ መስኖ የልማት ሥራዎችና በሌሎችም ዘርፎች የበኩሉን የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ ርእሰ መሥተዳድሩ አስረድተዋል።

የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ በማቋቋም፣ በድርቅ ምክንያት የተጎዱ ወገኖች በሚደገፉበት ሁኔታ ላይ ሀገራዊ ኀላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

አመልድ ኢትዮጵያ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲችል ከጠቅላላ የጉባኤው አባላት ታላቅ እገዛ ይጠይቃል ነው ያሉት።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/