ነዋሪነታቸው በኖርዌይ የሆነው ኢትዮጵያዊ አስማማው ተሻማው በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰበት አሚኮ የካሜራ ድጋፍ አደረጉ፡፡

0
319

ባሕር ዳር፡ ጥር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አቶ አስማማው ተሻማው ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ከመጡ በኋላ በተዘዋወሩባቸው የክልሉ አካባቢዎች አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የፈፀማቸውን ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳቶች ተመልክተው ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው ቡድን በተጠና መልኩ የማውደም ሥራ እንደፈጸመ መታዘባቸውን አንስተዋል፡፡

አቶ አስማማው “በክልሉ የደረሰዉን ሁሉን አቀፍ ጉዳት እያየን የምናልፍበት ሞራል ሊኖር አይገባም፤ የወደሙ ተቋማትን በፍጥነት ገንብተን ወደ ነበርንበት ከፍታ ልንመለስ ይገባል” ነው ያሉት፡፡

በደረሰብን ጉዳት መቆዘም ሳይሆን አጋጣሚውን እንደመነሻ መጠቀም ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ኤፍ ኤም 87.9 በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ውድመት እንደደረሰበት ከሚዲያው በመስማታቸው ድጋፉን እንዳደረጉ ገልጸዋል፡፡

ድጋፉን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥዬ ተረክበዋል፡፡ ሥራ አስፈጻሚው ለተደረገዉ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ቻይና አየልኝ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/