ትክክለኛ መረጃን በፍጥነት ለኅብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን መከላከል እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ተናገሩ፡፡

104

ባሕር ዳር: የካቲት 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሬድዮ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ጋር በመተባበር ዓለም አቀፉ የሬዲዮ ቀንን እያከበሩ ነው፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በዚህን ወቅት ሬድዮ ሕብረተሰቡን በማንቃትና መረጃን ተደራሽ በማድረግ በኩል ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡
በተለይ በኢትዮጵያ በርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለመረጃ ተደራሽ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወቱንም አንስተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃን በማሰራጨት በአገር ብሎም በሕዝብ ሰላምና መረጋጋት ላይ ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህንን ድርጊት በሕግ አግባብ ለማስተካከል ከሚደረገው ጥረት ባሻገር መገናኛ ብዙኀን ትክክለኛ መረጃን በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን መከላከል እንደሚጠበቅባቸው ነውበ የተናገሩት፡፡
ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ11ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡ ዘገባው የኢዜአ ነው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/