ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ አሜሪካን ጨምሮ ዓለም አቀፍ አካላት ለአፍሪካ ሕብረት ሚና ቅድሚያ እንዲሰጡ የአሜሪካ “ብላክ ኮከስ” አባላት ጠየቁ፡፡

0
62

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ አሜሪካን ጨምሮ ዓለም አቀፍ አካላት ለአፍሪካ ሕብረት ሚና ቅድሚያ እንዲሰጡ
የአሜሪካ “ብላክ ኮከስ” አባላት ጠየቁ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ ኮንግረስ የብላክ ኮከስ አባላት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን
በተመለከተ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ትብብር እና ሰላማዊ ድርድር ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ጠይቋል፡፡ እነዚህ ድርድሮች
በጋራ ጥቅም ፣ በእምነት እና በዓለም አቀፍ ሕግ መርሆዎች ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡
በቢሊዮኖች ዶላር ወጪ እየተገነባ ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት 6 ሽህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል
የሚያመነጭ ትልቁ የአፍሪካ የኃይል ማመንጫ ግድብ በመሆኑ ለቀጣናው ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን መግለጫው ጠቅሷል፡፡
ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ጎረቤት ሀገራት እንድትልክ ጭምር ያስችላታል ብሏል፡፡
ኮከሱ አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ አካላት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በ2015 (እ.አ.አ) የተፈራረሙትን ስምምነት
በማክበር እና ለአፍሪካ ሕብረት እና ለቀጣናው ዲፕሎማሲዊ ድርድር ቅድሚያ በመስጠት ገለልተኛ ሚና ሊጫወቱ ይገባል
ብሏል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ሰላማዊ ስምምነት ማድረግ ያለውን ጠቀሜታ በማጉላት ረገድ ወሳኝ ሚና
አለው ብሏል ኮከሱ በመግለጫው፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ፣ የግብፅ እና የሱዳንን የውኃ ፍሰት ፣ የኃይል አቅርቦት በማሻሻል እና
የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ያለውን ቀጥተኛ እና አዎንታዊ አስተዋጽዖ ኮከሱ በመግለጫው አብራርቷል፡፡
የግብፅ ሕዝብ ቁጥር በፍጥነት እጨመረ መምጣቱን ያነሳው መግለጫው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የውኃ
አቅርቦቱን ለማሻሻል ጠቀሜታው የጎላ ነው ብሏል፡፡
የኮከሱ መግለጫ ለኢትዮጵያም ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከድህነት መውጫ መንገድ መሆኑን አብነቶችን ጠቅሷል፡፡
ባለፈው መስከረም አካባቢ በኢትዮጵያ ተከስቶ ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ ሰብሎችን ያወደመው የአንበጣ መንጋ መከሰት ተደምሮ
ወደ 20 በመቶ የሚጠጋ የሕዝቧን ቁጥር በቀጥታ ይነካል ተብሎ የሚጠበቅ ድርቅ ተጋርጦባታል ብሏል፡፡
ለሱዳን የተስተካከለ የውኃ ፍሠት እንዲኖር በማድረግ ከዚህ በፊት ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትል የነበረውን ጎርፍ አደጋ በመቀነስ
ረገድ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚያበረክተውን አዎንተዊ አስተዋጽዖ አስረድቷል፡፡
ሱዳን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በግብርና ፕሮጀክት መስፋፋት እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ረገድም ተጠቃሚ
ትሆናለች ብሏል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቀጣናውን ኢኮኖሚያዊ እድገት በማፋጠን ረገድ ያለውን ጉልህ ድርሻ በመረዳት በጋራ መቆም
እንደሚገባ ኮከሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ኮከሱ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡
በየማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here