ብራና ማተሚያ ድርጅት ለተፈናቀሉ ወገኖች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ።

0
30
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ብራና ማተሚያ ድርጅት የማኔጅመንት አባላት እና ሠራተኞች ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
ድጋፉን ያስረከቡት በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ብራና ማተሚያ ድርጅት ባለሙያ ወይዘሮ እቴነሽ ለማ እንደገለፁት ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ለወገን ያለንን ደራሽነት ለመግለጽ የተደረገ ድጋፍ ነው ብለዋል። ሁሉም አካል ተፈናቃዮችን በመደገፍ ረገድ መረባረብ እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የብራና ማተሚያ ድርጅት የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ሥራ አስኪያጅ በለጠ ጸጋዬ እንደተናገሩት የማኔጅመንት አባላት እና ሠራተኞች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በመሰብሰብ ለሕጻናት፣ ለነፍሰ ጡር እናቶች እና ለአዛውንቶች የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
የተቃጣብንን ወራራ ለመመከት እና ችግሩን ለመሻገር በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ሥራ አስኪያጁ።
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ባለሙያ ጥላሁን አምበሉ ስለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ነጻ በወጡ አካባቢዎች እርዳታ የሚፈልጉ በርካታ ወገኖች ስለሚገኙ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation