ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሁለት የሀገር ባለውለታዎች የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ ነው፡፡

0
289

ባሕር ዳር፡ መስከረም 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀጣዩ ቅዳሜ በሚያካሂደው የ2013 ዓ.ም የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ስርዓት ለሁለት እውቅ የሀገር ባለውለታዎች ማለትም፡

በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት መከበር፣ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ብሎም ለፍትሕና እኩልነት መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ለሚታወቀውና ለኢትዮጵያዊነት
አቀንቃኙ አቶ ኦባንግ ሜቶ እንዲሁም በኢትዮጵያና ሌሎች በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ህጸተ-ዝናብ አካባቢዎች በሰሯቸው የምርምር፣ የልማትና አቅም ግንባታ ሥራዎችና ባመጧቸው አወንታዊ ለውጦች ለሚታወቁት ታላቁ ጃፓናዊ ፕሮፌሰር አሱሺ ሱኔካዋ
የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ይሸልማል፡፡

ዩኒቨርሲቲውም የ2013 ዓ.ም የክብር ዶክትሬት ተሸላሚዎች አቶ ኦባንግ ሜቶ እና ፕሮፌሰር እሱሺ ሱኔካዋ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m