ባለሃብቱ ለመከላከያ ሠራዊት፣ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ለሚሊሻ እና ለፋኖ ድጋፍ አደረጉ፡፡

0
122

ባሕር ዳር: ነሐሴ14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በቲሊሊ ከተማ ነዋሪ አቶ ዘመኑ ጥላዬ የተባሉ ባለሃብት የሕልውና ዘመቻውን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ግንባር ላይ ለሚገኙት ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይል፣ለሚሊሻ እና ለፋኖ ደረቅ ሬሽን ለግሰዋል፡፡ ድጋፉንም የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ተረክቧል።

ሬሽኑን ያስረከቡት የባለሃብቱ ወንድም ወጣት አብርሃም ጥላዬ ከ300ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ደረቅ ሬሽን ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት። በቀጣይም ለህልውና ዘመቻው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የባለሃብቱን ድጋፍ የተረከቡት የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ባይነሳኝ ዘሪሁን ባለሃብቱ ላደረጉት አኩሪ ተግባር ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ባለሃብቱ ከዚህ በፊት ለመከላከያ ሠራዊት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ ስዩም መስፍን (ዶክተር) በበኩላቸው ”እንደ ሀገር የተቃጣብንን የህልውና አደጋ ለመመከት የባለሃብቱ ሚና ወሳኝ በመሆኑ የተደረገው ድጋፍ ሌሎች ባለሃብቶችን የሚያነሳሳ አርዓያ ያለው ተግባር ነው” ብለዋል።

ፎቶ፡- በተስፋሁን ደስታ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here