ባለሀብቱ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረጉ።

0
195

ደሴ፡ መስከረም 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይተነው ከሰሜን ወሎ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ጎብኝተዋል። አቶ ወርቁ ለተፈናቃዮች እንዳሉት አሸባሪው ትህነግ አማራን በመግደል፣ በመዝረፍና በማፈናቀል ያለውን ጥላቻ እያሳየ ይገኛል።

በዚህ የሽብር ቡድን ከሰሜን ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያሉባቸውን ችግሮች በመለየት ደጀን ለመሆን መገኘታቸውን ገልጸዋል።

ተፈናቃይ ወጣቶችም በመደራጀት ባፈናቀላቸው አሸባሪ ቡድን ላይ መዝመት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የመንግሥት አካላትም ወጣቱን የማደራጀት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አንስተዋል። በተለይም ደግሞ ወደ ሀገር መከላከያ ተቋም መቀላቀል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

በሽብር ቡድኑ የተወረሩ አካባቢዎች ነጻ ኾነው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እስኪመለሱም ሁሉም እንደ አቅሙ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሰራ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m