በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መገናኛ ብዙኀን ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው የሰላም ሚኒስቴር አሳሰበ።

160

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መገናኛ ብዙኀን ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው የሰላም ሚኒስቴር አሳሰበ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 26/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መገናኛ ብዙኀን በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ እና በድህረ
ምርጫ ወቅት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚስቴር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ
ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ መገናኛ ብዙኀን ሕዝብና ሀገርን የሚያሻግር ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል። መገናኛ ብዙኀን
ከአሉባልታና ከሀሰተኛ መረጃ በመራቅ ትክክለኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለሕብረተሰቡ የመስጠት ኀላፊነታቸውን እንዲወጡም
አሳስበዋል።
የምርጫ አስፈጻሚ አካላት በምርጫ ወቅት ለብዙኀን መገናኛ በወቅቱ መረጃ የመስጠት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሃመድ ኢድሪስ አሳስበዋል።
የባለ ስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በቅድመ ምርጫ ወቅት መገናኛ ብዙሃን የሕግ እና የሞራል ኀላፊነት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።
የመገናኛ ብዙኀን ኀላፊነታቸውን ከተወጡ፣ ምርጫው በሰላም ከተከናወነ እና ሕዝቡ በምርጫ የስልጣን ባለቤት ከሆነ ኢትዮጵያ
ታሸንፍለች ብለዋል ዳይሬክተሩ።
መገናኛ ብዙኀን ከየትኛውም አካል የሚደርስባቸውን ተጽዕኖ ተቋቁመው ለሕዝብ ትክክለኛ መረጃ መስጠት እንዳለባቸውም
ገልጸዋል።
በውጭ ቋንቋ የሚሠሩ መቀመጫቸውን በሀገር ውስጥ ያደረጉ መገናኛ ብዙኀን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ መረጃ
ከማሰራጨት መቆጠብ እንዳለባቸውም ነው በውይይቱ ላይ የተነሳው ።
በተለይም በድህረ ምርጫ ወቅት ለግጭት የሚጋብዙና ለቀውስ የሚዳርጉ መረጃዎች ላይ መገናኛ ብዙኀን በከፍተኛ ኀላፊነት
እንዲሠሩ ተጠይቋል።
የሰላምሚኒስቴር የመገናኛ ብዙኀን ሚና በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር
የምክክር መድረክ አካሂዷል።
ዘጋቢ:–ዳንኤል መላኩ– ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m