በ፩ኛው የአማራና ኪነ ጥበብ ጉባኤ ማጠቃለያ በኪነ ጥበብና ሥነ ጥበብ ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ዕውቅና ተሰጣቸው፡፡

264
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ

በ፩ኛው የአማራና ኪነ ጥበብ ጉባኤ ማጠቃለያ በኪነ ጥበብና ሥነ ጥበብ ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ዕውቅና ተሰጣቸው፡፡

ከጥቅምት 22-23 በባሕር ዳር ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያው የአማራና ኪነ ጥበብ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቅቋል፤ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩም አንጋፋ የኪነ ጥበብና የሥነ ጥበብ ሰዎች ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በሁለት ዘርፍ በነበረው የዕውቅና ሥነ ሥርዓት የዋንጫና የካባ ስጦታ ለተሸላሚዎች ተበርክቷል፡፡

በድርሰት፣ በስዕልና ቅርጻ ቅርጽ፣ በሙዚቃ፣ በታሪክና ልቦለድ ጸሐፊነት በርካታ ከያንያን ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ የአፍሪካ ጃዝ ሙዚቃ ፈጣሪው ሙላቱ አስታጥቄ፣ ጸሐፌ ተውኔትና ገጣሚ አያልነህ ሙላቱ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ አጥናፍሰገድ ይልማ፣ አስፋው ዳምጤ፣ ደበበ እሸቱ፣ የዱርፍሬ ይፍሩ፣ ገስጥ ተጫኔ እና ፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁ በርዕሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የዕውቅና ካባ ለብሰዋል፡፡ የታሪክ መምህሩ ታዬ ቦጋለም ልዩ ተሸላሚ ሆነው ካባ ለብሰዋል፡፡

አንዳርጌ መስፍን፣ እሸቱ ጥሩነህ፣ ተክሌ ደስታ፣ ጌታቸው በለጠ፣ ስዩም ተፈራ፣ ችሮታ ከልካይ፣ ጌትነት እንየው እና ሌሎችም በዕለቱ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

የኪነ ጥበብና የሥነ ጥበብ ባለሙያዎቹ ሙያቸውን መሠረታዊ መርሁን ሳይለቅ ለእውነትና አብሮነት መሠረት ሆኖ እንዲቀጥልና የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት አጋዥ እንዲሆን እንደሚተጉ ቃል ገብተዋል፡፡

በየዘርፎቹ ተጠሪዎችን በመሠየምም ኮሚቴ አዋቅረው በቀጣይነት ማኅበራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡ በሁለት ቀናት ምክክራቸው የደረሱበትን መግባባት የሚያፀባርቅ የአቋም መግለጫም አውጥተዋል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህም መንግሥት ለዘርፉ አስፈላጉውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡ ኪነ ጥበብን ለመልካምነት ማስተጋቢያና አብሮነት ማጠናከሪያ እንዲጠቀሙም አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አብርሃም በዕውቀት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here