“በፓን አፍሪካዊ አስተሳሰብ የተፀነሰው የአፍሪካ ህብረት”

0
36

አዲስ አበባ: ጥር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጊዜው 1955 ዓ.ም ግንቦት ወር ላይ ነው፡፡ 32 ነጻ የአፍሪካ ሀገራት አህጉራዊ ጉዳያቸውን በራሳቸው የሚነጋገሩበትና ለመፍትሔ የሚበቁበትን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሰረቱ፡፡ ድርጅቱ ከ36 ዓመታት ቆይታ በኋላ ደግሞ ስሙን ወደ አፍሪካ ህብረትነት ቀይሮ 55 ሀገራትን አቅፏል፡፡

በፓን አፍሪካዊ አስተሳሰብ የተፀነሰው ይኸው ተቋም አፍሪካውያንን ከቅኝ ግዛትና ባርነት አላቆ የበለፀገች አፍሪካን የመፍጠር ዓላማ ይዞ ቀጥሏል፡፡ ረጂም ጉዞን በውጭ ጣልቃ ገብነት የሀገራት እርስ በእርስ ግጭቶችና ፈተናዎች ቢገጥሙትም ዛሬም እንደሌሎች ህብረቶቸ ሁሉ ለአባል ሀገራቱ አፍሪካዊ መፍተሔ እየሰጠ 35ኛው የመሪዎች ጉባኤው ላይ ደርሷል፡፡

የኮሮናቫይረስ እና የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ ስብሰባው በአካል በአዲስ አበባ እንዳይደረግ ጫናዎች ሲደረጉ ቢቆዩም ጉባኤውን በአዲስ አበባ ለማድረግ በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ውጣ ወረዶች ታልፈው ጉባኤው መቀመጫ ሀገሩ ላይ እንደተለመደው “የተመጣጠነ ምግብ እና የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል፡፡

የህብረቱ ውሳኔ ቁርጠኝነትን የሚያሳይ እና አፍሪካውያን በአንድነት ለራሳቸው መፍትሔ ለማድረግ መነሳታቸውን እንደሚያሳይም በአሜሪካን ሀገር ካሮላይና ግዛት ኤ ኤንድ ቲ ስቴት ዩንቨርስቲ የፖለቲካ እና ጋዜጠኝነት መምህሩን ፕሮፌሰር ብሩክ ሀይሉ ገልጸዋል።

ጉባኤው የኢትዮጵያ ጠላቶች ኮሮናን በዋናነት ሽፋን በማድረግ እና ሰላም የለም፣ ከተማዋም የመሪዎችን ጉባኤ ለማድረግ አትመችም በማለት በአካል በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ በርካታ ተንኮሎችን ቢሰሩም የአፍሪካ መሪዎች ባሳዩት ቁርጠኝነትና ይህን ተንኮል ለማፍረስ በተሰራው ዲፕሎማሲያዊ ስራ ተሳክቷል ያሉት ፕሮፌሰር ብሩክ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጠቀሜታው ብዙ ነው ብለዋል፡፡

ምእራባውያኑ በተለያዩ መንገዶች ኢትዮጵያ ላይ ሲያሳርፉት የነበረው ጫና እንዳልተሳካ ማሳያ ከመሆኑም በላይ ለዓለም ብዙ መልእክት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ይህ ጉባኤ እንደ ሌሎች ትዕይንቶች ኢትዮጵያ ሰላሟን ለዓለም የምታረጋግጥበት፣ በፈተናዎች ውስጥ ብታልፍም አሸናፊ መሆኗን የምታሳይበት ነው ብለዋል ፕሮፌሰር ብሩክ።

ኮሮናቫይረስን እና የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ ስብሰባው በአካል በአዲስ አበባ እንዳይደረግ ጫናዎች ቢደረጉም ጉባኤው እንዲካሄድ መሪዎች መወሰናቸው ህብረቱ ቁርጠኛ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል የፖለቲካ እና ጋዜጠኝነት መምህሩ ፕሮፌሰር ብሩክ ኀይሉ፡፡

ዘጋቢ:–አብነት እስከዚያ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/