በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቀ።

0
329

ጥር 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር የተፈጸመውን ሕገወጥ ድርጊት በመቃዎም መግለጫ አወጥቷል።

ጉባኤው በመግለጫው ሃይማኖቶች የትህትና፣ የሰላምና የአንድነት፣ የፍቅርና መከባበር መሠረቶች ናቸው ብሏል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የሰላም መሠረት ሆና ዘልቃለች ያለው የጉባኤው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን አጥብቀን እንቃዎማለን ነው ያለው።

ጥር 12/2014 ዓ.ም በቡራዩ ከተማ አስተዳደር በሕግ ማስከበር ሽፋን በቤተክርስቲያኗ ላይ የተቃጣው ድርጊት ፍጹም ሕገ ወጥ ነው ያለው መግለጫው መንግሥት አጥፊዎችን ተከታትሎ ለሕግ እንዲያቀርብም ጠይቋል።

መንግሥት የሃይማኖትን እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቀው የጉባኤው መግለጫ የሕይዎት፣ የአካል እና የመንፈስ ስብራት በደረሰባቸው ወገኖች የተሠማንን ጥልቅ ሐዘንም በተሰበረ ልብ እንገልፃለን ነው ያለው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/